ቻይና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በራሱ በመጠቀም የሚሽከረከረውን ስማርት የከባድ ጭነት ተሽከርካሪ ሙከራ በተሳካ ሁኔታ አጠናቀቀች።ፋው ጄፋንድ አውቶሞቲቭ የተባለው መኪና አምራች ኩባንያ በቻንግቹን ሸንዘን የፍጥነት መንገድ ላይ ሶስት ስማርት ተሽከርካሪዎች በራሳቸው እንዲሽከረከሩ ያደረገው ሙከራ የተሳካ መሆኑን ገልጿል።የከባድ ጭነት ተሽከርካሪው 40 ቶን ክብደት የመጫን አቅም ያለው ሲሆን፥ ለማቋረጥ፣ ለመታጠፍ እና ፍጥነት ለመጨመር የሚያስችል አውቶማቲክ ቴክኖሎጂ ተገጥሞለታል።ከሰው እጅ እርዳታ ውጭ መሪን በአግባቡ ለመጠቀም የሚያስችል ስርዓትም አለው ነው የተባለው።የፋው ጄፋንግ አውቶሞቲቭ ኩባንያ ጄነራል ማናጀር በቴክኖሎጂ ታግዘው የሚጓዙ ስማርት ተሽከርካሪዎች፥ በቀጣይ ዓመታት አሁንላይ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙትን ተሽከርካሪዎችን እንደሚተኩ ተናግረዋል።ኩባንያቸው በፈረንጆቹ 2018 ከፍተኛ ብቃት እና ጥራት ያለው ሞዴል እንደሚያመርት የገለፁ ሲሆን፥ በ2020 ደግሞ በአምስተኛ ትውልድ የኔትወርክ ተግባቦት የሚሰራ ተሽከርካሪን ያመርታል ብለዋል።በ2025 የመጀመሪያውን አሽከርካሪ አልባ መኪና ለማምረት ማቀዱንም ነው የጠቆሙት።ኩባንያው የመጀመሪያውን ቻይና ሰራሽ ተሽከርካሪ በ1956 ያመረተ ሲሆን፥ ከዚያ ወዲህ 6 ሚሊየን መኪናዎችን አምርቷል።በተያዘው 2017 ባለፉት 9 ወራትም፥ 198 ሺህ መኪናዎችን በመሸጥ በቻይና ቀዳሚውን ስፍራ ይዟል።
አይናችን ስለ ጤናችን ምን ይናገራል? አይኖቻችን አለምን ከማስመልከት ባለፈ ስለጤናችንም ብዙ ይናገራሉ። በአይኖቻችን ላይ የሚታዩ ለውጦች የእይታ ችግር፣ የስኳር በሽታ፣ ጭንቀት እና መሰል ችግሮች መጋለጥን ሊያሳዩ ይችላሉ።የአሜሪካ የአይን ህክምና አካዳሚ ቃል አቀባይ ዶክተር ናታሻ ሄርዝም አይናችን ስለ ጤናችን የሚናገሩት በርካታ ነገር አለ ይላሉ። በአይናችን የሚታዩ ያልተለመዱ ምልክቶችን ማስተዋል ከቻልን የችግሩን ምንጭ በመረዳት ለመፍትሄው መንቀሳቀስ እንጀምራለን። ከዚህ በታች የተዘረዘሩት በአይናችን ላይ የሚታዩ ምልክቶች ስለ የሚሉት እንዲቀህ ቀርቧል። 1. የአይን ቆብ እብጠት በአይን ቆብ ላይ የሚወጣ እብጠት መጠነኛ የህመም እና የማቃጠል ስሜት ሊኖረው ይችላል፤ ብዙ ጊዜ በጥቂት ቀናት ውስጥም ይጠፋል። ይሁንና እብጠቱ ከአይናችን ቆብ ላይ እስከ ሶስት ወራት ድረስ የማይጠፋ ከሆነ ላልተለመደው “ሳባካሲየስ ግላንድ ካርኪኖማ” ካንሰር መጋለጥን ሊያመላክት ይችላል። በተመሳሳይ ቦታ ለረጅም ጊዜ በአይን ቆባችን ላይ የሚወጣ እብጠትም ከላይ ለጠቀስነው የካንሰር አይነት ተጋላጭ መሆንን ሊያሳይ እንደሚችል ተገልጿል። 2. የቅንድብ ፀጉር መርገፍ የቅንድብ ፀጉር በተለያዩ ምክንያቶች ሊረግፍ ይችላል። የቅንድባችን ጫፍ (ሳሳ ያለው ክፍል) ፀጉር መርገፍ ከጉሮሮ ጋር ለተያያዘ ችግር መጋለጣችን ያሳያል። የአይን ሽፋሽፍት ፀጉር መርገፍ ደግሞ ለካንሰር ከመጋለጥ ጋር ሊያያዝ ይችላል ተብሏል። 3. የአይን መርገብገብ ጭንቀት ከሚንፀባረቅባቸው መንገዶች አንዱ የአይን መርገብገብ ነው። ብዙ ጊዜ አይናችን የሚርገበገብ ከሆነ ለጭንቀት መጋለጣችን ያመለክታል የሚሉት ዶክተር ሄርዝ፥ በመሆኑም በቂ እረፍት ማግኘት ይሆርብናል ብለዋል። 4. የእይታ ብዥታ – ስኳር አይ...
Comments
Post a Comment