#ው ሸ ታ ም
እሷ የደም እሳት የላት
አኮ ትዝታኮ ለካ፥ ከቶውኑ ቅድስት ናት
ምንም ሕመም እይሰማት
እሷን የእግዜር ፍቅር እንጂ የሰው አሳቱም አይሞቃት
ብቁ ናት ለካ ፍጹም ናት።
#አነሱራፌል ኪሩቤል በእሳት ሠረገላ ወርደው
በመለኮት ብርሃን አቅፌው
በአክናፋት አኮቴት ቀዝፈው
በኅብር አዝለው አንከባክበው
ሰባቱን ሰማያት መጥቀው
ሽቅብ ይዘው ሽቅብ ይዘው
#አዎ ትዝታኮ ለካ
በሥጋዊ ልቡሰ ሕመም ሳትወስን ሳትለካ
በምድር ሰሜት ሳትነካ
በሰው መውደድ ሳትረካ
#ቅዱሰ መንፈስ ያለበሳት
ብቁ ናት ለካስ ፍጹም ናት
ያሰው እሳት እማይሞቃት
#ከመላእክት ጋር አብራ ክንፍ አውጥታ ተፈትልካ
ምንም ምንም ሳትነካ
በቃች ትዝታኮ ለካ
#ሰው አደለችም ቅዱሰ ናት
የሰው ንዳድ እማይሞቃት
#ብቁ ነች አዎ ፍጹም ነች
ምን ያረጋል ሰው አደለች።
#እሷ የደም እላት የላት
እውነት የእውነት ውሸታም ናት።
Comments
Post a Comment