ቻይና በግዛቷ የሚገኙ የሰሜን ኮርያ የንግድ ተቋማትን ልዘጋ ነው አለች
BBN መስከረም 18/2010
የቻይና መንግስት በሀገሩ የሚገኙ የሰሜን ኮርያ የንግድ ተቋማትን ሊዘጋ መሆኑን አስታወቀ፡፡ ይህን እርምጃ ለመውሰድም የ120 ቀናት ጊዜ ተቀምጧል፡፡ በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ውስጥ በቻይና የሚገኙ የሰሜን ኮርያ የንግድ ተቋማት ሙሉ በሙሉ እንደሚዘጉ ሮይተርስ የቻይና ባለስልጣናትን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ የቻይናን የንግድ ሚኒስቴር ዋቢ ያደረገው ዘገባው፣ እርምጃው ቻይና ከሰሜን ኮርያ ጋር በጋራ የምታካሂደውን የንግድ ተቋማትን ጭምር እንደሚያካትት ገልጿል፡፡
ቻይና ይህን እርምጃ የምትወስደው ሰሜን ኮርያ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ ምክንያት በማድረግ ነው፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በፈረንጅ አቆጣጠር መስከረም 12 ቀን 2017 በሰሜን ኮርያ ላይ የተለያዩ ማዕቀቦችን የጣለ ሲሆን፣ አንደኛው ማዕቀብ የሰሜን ኮርያን የንግድ ተቋማት የሚመለከት ነው፡፡ የማዕቀቡን የውሳኔ ሀሳብ ያቀረበችው አሜሪካ ስትሆን፣ ማዕቀቡም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት አባላት በሙሉ ድምጽ ጸድቋል፡፡
ማዕቀቡ ሰሜን ኮርያ የነዳጅ ምርቶችን ወደ ሀገሯ እንዳታስገባ ከመከልከል አንስቶ፣ ሀገሪቱ ወደ ውጭ የምትልካቸው የጨርቃ ጨርቅ ምርት ላይ ክልከላ እስከማድረግ ይዘልቃል፡፡ የጸጥታው ምክር ቤት በሰሜን ኮርያ ላይ ማዕቀብ ለመጣል ምክንያት አድርጎ የወሰደው፣ ሀገሪቱ በተደጋጋሚ ጊዜ የኑክሌር ሙከራ ማድረጓን ነው፡፡ ሰሜን ኮርያ ባለፈው ለስድስተኛ ጊዜ የሃይድሮጂን ቦንብ ሙከራ ማድረጓ፣ ማዕቀብ እንዲጣልባት መንስኤ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል፡፡ የሰሜን ኮርያው ጎረምሳ መሪ እና የአሜሪካው አዛውንት ፕሬዚዳንት፣ የኑክሌር ቦንብ ሙከራን በተመለከተ ኃይለ ቃል ሲወራረወሩ መሰንበታቸው ይታወሳል፡፡

Comments
Post a Comment