የኢራቅኩርዶች በሰሜናዊ ኢራቅ የሚገኘው የኩርዲስታን ግዛት ነፃ ሀገር እንዲሆን
የኢራቅኩርዶች በሰሜናዊ ኢራቅ የሚገኘው የኩርዲስታን ግዛት ነፃ ሀገር እንዲሆን የተካሄደውን ህዝበ ውሳኔ በመደገፍ ድምጽ ሰጡ።በሰሜናዊ ኢራቅ የሚትገኘው ከፊል ራስ ገዝ የሆነው የኩርዲስታን ግዛት ነጻ ሃገር ለመሆን ባለፈው ሰኞ ህዝበ ውሳኔማካሄዱ ይታወሳል።በህዝበ ውሳኔው ላይ ድምጽ የሰጡ የኢራቅ ኩርዶችም፥ ከፊል ራስገዝ አስተዳደሩ ነጻ ሃገር ይሆን ዘንድ የሚያስችለውን ድምጽ ሰጥተዋል።ከ3 ነጥብ 5 እስከ 5 ሚሊየን የሚጠጉ ኩርዶች በተሳተፉበት ህዝበ ውሳኔ፥ 92 በመቶዎቹ ራስ ገዝ አስተዳደሩ ነጻ ሃገር ይሆን ዘንድ ደግፈው ድምጽ ሰጥተዋል።የኢራቅ ኩርዶች መሪ የሆኑት መስዑድ ባርዛኒ፥ ውጤቱን መሰረት አድርገው በአስቸኳይ ነጻነታቸውን እንደማያውጁ ተናግረዋል።ከዚያ ይልቅ ከኢራቅ መንግስት ጋር እንደሚደራደሩ ነው የተናገሩት።ህዝበ ውሳኔው ህገ መንግስቱን የሻረና ህገ ወጥ ነው ያለው የኢራቅ መንግስት በበኩሉ፥ ማንኛውንም የኩርድ ነጻ ሃገር የመመስረት ሃሳብ እንደማይቀበል በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል።ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይደር አል አባዲም፥ የህዝበ ውሳኔው ውጤት ከመንግስታቸው ጋር ለመደራደሪያነት እንደማይቀርብ ገልጸዋል።የሚደረጉ ውይይቶችም የሃገሪቱን ህገ መንግስት በተከተለ መልኩእንደሚሆኑም አጽንኦት ሰጥተዋል።በኢራቅ የኩርዲስታን ግዛትም የኢራቅ ህገ መንግስት ይተገበራልብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።የኢራቅ ፓርላማ በበኩሉ በነዳጅ በበለጸገችው የኪርኩክና በሌሎች አወዛጋቢ የኩርዲስታን አካባቢዎች ወታደር እንዲሰፍር እየጠየቀ ነው።ምንጭ፦ አልጀዚራና ቢቢሲ
Comments
Post a Comment