ጠፈር
አውስትራሊያ ከፍተኛ ገቢ የሚያስገኝ እና በፍጥነት እያደገ ላለው የጠፈር ምርምር
የሚያግዝ ብሄራዊ የጠፈር ተቋም ልትገነባ መሆኑን አስታወቀች።ሀገሪቱ ዓለም አቀፍ ታላላቅ ሳይንቲስቶች እና ባለሙያዎች በተሳተፉት የአደላይድ የጠፈር ኮንፈረንስ ላይ ነው ይህን እቅድ ይፋ ያደረገችው።በሀገሪቱ እና በዓለም አቀፍ የጠፈር መርሃ-ግብር ውስጥ ከፍተኛአስተዋፅኦ ያለው ይህ ተቋም፥ ካንቤራ ከሌሎች የበለጸጉ ሀገራት ጋር እንድትስተካከል ያደርጋታል ተብሏል።በተጨማሪም ኢንዱስትሪ ለማቀናጀት እና የልማት እድገትን ለማገዝ የራሱ አስተዋፅኦ አለው ነው የተባለው።የአውስትራሊያ የሳይንስ ሚኒስቴር ፥ ዓለም አቀፍ የጠፈር ምርምር ኢንዱስትሪ እያደገበት ባለው ዘመን ሀገሪቱ ከዚህ እኩል ዘርፉን ማሳደግ እንደሚገባት ነው የጠቆመው።“ብሔራዊ የጠፈር ተቋሙ፥ የአረንጓዴ ቴክኖሎጂን እድገት እና ተግባራዊነት የሚደግፍ ስትራቴጂያዊ የረጅም ጊዜ ዕቅድ እንዳለን የሚያሳይ እና የአካባቢያችን ኢንዳስትሪ እንዲዳብር የሚያግዝ ነው፤” ሲል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል።የሀገሪቱ መንግስት የፀጥታ፣ የመከላከያ እና የቴሌኮሙዩኒኬሽን አገልግሎትን የሚያጠቃልለው ዓለም አቀፋዊ የጠፈር ዘርፍ፥ በአውሮፕያኑ አቆጣጠር ከ1990ዎቹ ጀምሮ 10 ከመቶ ገደማ እድገት እያሳየ መምጣቱን ገልጿል።በዚህመ በየዓመቱ 323 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ እያስገኘ ነው።አውስትራሊያ ከአሜሪካ እና ሩሲያ ቀጥሎ ሶስተኛ ሀገር የሆነችበትንና፥ የመጀመሪያውን ሳተላይት ይፋ ያደረገችበትን 50 ዓመት በያዝነው የፈረንጆች ዓመት ታከብራለች።ለበርካታ አሥርተ ዓመታት በአብዛኞቹ የጠፈር ስራዎች ውስጥ የዓለማቀፍ ጥልቅ ቦታዎችን ለመከታተል ከሚችሉ ሶስት ቦታዎች አንዱ በካንቤራ የሚገኝ ሲሆን፥ በናሳ የጠፈር ምርምር ወሳኝ ሚና ተጫውቷል ነው የተባለው።ምንጭ፦ ሲ.ጂ.ቲ.ኤን.

Comments
Post a Comment