አለም እንዴት ዋለች

በኢራቅ የኩርዲስታን ግዛት ነፃ ሀገር የመሆን አለመሆን ጥያቄ ላይ ህዝበ ውሳኔ መካሄዱን ተከትሎ የቱርክ እና የኢራቅ ወታደሮች የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ማድረግ ጀምረዋል።በሰሜናዊ ኢራቅ የምትገኘው በከፊል ራስ ገዝ የሆነችው የኩርዲስታን ግዛት ህዝበ ውሳኔውን ማካሄዷ 14 ሚሊየን ኩርዶችን የያዘችውን ቱርክ አበሳጭቷል።የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶኻንም ነፃ አገር የመመስረት ፍላጎትን ወደ ተግባር ለማሸጋገር ከተሞከረ አገራቸው በዝምታ እንደማታልፍ ተናግረው
ነበር።የአገራቸው ጦርም ለዚህ ዝግጁ መሆኑንም ነው የገለፁት።አሁን በሁለቱ አገራት ድንበር ላይ የተጀመረው የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ለህዝበ ውሳኔው የተሰጠ ምላሽ ተደርጎ ተወስዷል።ምንጭ፦ አልጀዚራ

Comments

Popular posts from this blog

ሳይኮሎጂ